የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚሰለፉ አረጋገጡ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ሐምሌ 18 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ “ኢትዮጵያን ማፍረስ አይቻልም ። ምክ…

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚሰለፉ አረጋገጡ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ሐምሌ 18 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ “ኢትዮጵያን ማፍረስ አይቻልም ። ምክንያቱም ሰው አለ!!” በሚል መሪ ቃል በቀድሞ የሰራዊት አባላት የድጋፍና የልማት ማህበር አነሳሽነት በመስቀል አደባባይ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ የተገኙት የቀድሞ የሰራዊት አባላት በማንኛውም ግዳጅ ከሰራዊቱ ጎን እንደሚሰለፉ አረጋግጠዋል። በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ፣ የቀድሞ የሰራዊት አባላት ለሀገራቸው ካላቸው ፍቅር የተነሳ በግፍ በትኗቸው ከነበረው የህውሀት ቡድን ጋር ጭምር ሀገር ስትወረር ቀድመው በመሰለፍ በተለያዩ ወታደራዊ ሙያዎች ሀገራቸውን ማገልገላቸውን አስታውሰው ፣ አሁንም ሀገር በፈለገቻቸው ወሳኝ ወቅት በራሳቸው ተነሳሽነት ከሰራዊቱ ጎን ለመሰለፍ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል። የማህበሩ ሰብሳቢ አምሳ አለቃ ብርሀኑ አማረ ፣ የመከላከያ ሰራዊቱ ሀገርን ለመበታተን ከተነሱ ሀይሎች ጋር የሚያደርገውን ትግል በሙያቸው ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን እንደገለጹ የሀገር.መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ገጹ ላይ ዘግቧል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር በመላ ሀገሪቱ 287 ቅርንጫፍና ከአንድ ሚሊየን በላይ አባላት አሉት። ኢፕድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply