የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በቅፅል ስማቸው “ሻሾ” በሚል በስፖርት ቤተሰቡ በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም ከ1940ዎቹ መጨረ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/SV0otCXVZ6BiS0wLVYen0p36K5RcyoJwkSL9GlUqw2USwD59WaYhcC0KhzLtrI35JUKTHTjbV1jqVMYVwOs8iXv-k3-McjD_NzSlCvY2Vdy50zVLJlADnX6Ih_IeqRfKQQ-GQHgijDOUvMDO8wWo_R76F2u6RXn3g78EOlzzIja-7wlKW9x8ak6x-Zb5PFwC0o9LLrrYkTPMd9TSQI4WBVcVsCr4AsHfqR9dnI65tUJtycdsP4ME6Np7Yzcqm6Ubmgsa7sabKNwvXhslQMim2fW1Sxtd89uDn3DOGNiY9BZnuXaLcZ9cdi_UlbIA9QnTVRGP7j_XHZ_G67zjShY5XA.jpg

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በቅፅል ስማቸው “ሻሾ” በሚል በስፖርት ቤተሰቡ በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም ከ1940ዎቹ መጨረሻ እስከ 60ዎቹ መጀመርያ በነበረው የተጫዋችነት ህይወታቸው ለጥቅምት 23፣ ሸዋ ፖሊስ፣ ዳኘው እና ሸዋ ምርጥ የተጫወቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንንም በተለያዩ የእድሜ እርከኖች እና ዋናው ቡድን አገልግለዋል። በ1954 ኢትዮጵያ የሦስተኛው አፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍም የቡድኑ አባል ነበሩ።

የቀድሞ ተጫዋች ኃይለማርያም መኮንን ሥርዓተ ቀብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ-ክርስቲያን ዛሬ 6:00 ላይ ተፈፅሟል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም  107.8 በቀድሞ የብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋች ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና የእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

ምንጭ EFF

Source: Link to the Post

Leave a Reply