የቀድሞ የጋቦን ፕሬዚዳንት ልጅ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ተያዙ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-02f1-08dbb9eb9073_cx0_cy2_cw0_w800_h450.jpg

በቅርቡ በመፈንቅለ መንግሥት የተወገዱት የቀድሞ የጋቦን ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ኦንዲምባ ልጅና ሌሎች በርካታ ተባባሪዎች በሙስና ተከሰው በእስር ላይ እንደሚገኙ የአገሪቱ ዐቃቤ ህግ ዛሬ ረቡዕ ለኤኤፍፒ ተናገሩ፡፡

የቦንጎ የበኩር ልጅ ኑረዲን ቦንጎ ቫለንቲን እና የቀድሞ የፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ ጄሲ ኤላ ኤኮጋ በሙስና ወንጀል ተከሰው በጊዜያዊ እስር ላይ ይገኛሉ ሲል የሊብሬቪል አቃቤ ህግ አንድሬ-ፓትሪክ ሮፖናት ተናግረዋል፡፡

ከእ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ በነዳጅ የበለጸገቸውን ማዕከላዊ አፍሪካ አገር ሲመሩ የቆዩት የ64 ዓመቱ ቦንጎ፣ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸውን ካወጁ በኋላ ባለፈው ነሐሴ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወግደዋል፡፡

መፈንቅለ መንግሥቱ በተካሄደበት ዕለት ወታደራዊ መሪዎቹ አንዱን የቦንጎን ልጅ እና ሌሎች አምስት ከፍተኛ የካቢኔ አባላትን ማሰራቸው ይታወሳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply