የቀድሞ የጦር ተጎጂዎች አስከፊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ሳልሳይ ወያነ ትግራይ/ሳወት/ ገለጸ፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ የቀድሞ የጦር ተጎጂዎች በቂ የሆነ ህክምና እያገኙ አይደል መባሉን ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ሁለት ዓመት ባስቆጠረው ጦርነት የተሳተፉ የትግራይ ተወላጅ ተዋጊዎች ያሉበት ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል ፓርቲው ገልፃል፡፡

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኪሮስ ሀይለስላሴ ከጣብያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ የጦር ጉዳተኞቹ በተደጋጋሚ ሰልፎች ችግራቸው እንዲፈታ ቢጠይቁም ምላሽ ሊያገኙ አልቻሉም ብለዋል፡፡

ከግዚያዊ አስተዳደሩም ሆነ ከፌደራል መንግስት አጥጋቢ ምላሽ ሊገኙ እንዳልቻሉ ህዝብ ግኙነቱ ያስረዳሉ፡፡

የቀድሞ ተዋጊ የጦር ጉዳተኞች በቅርቡ በመቀሌ ዋና ዋና አደባባዮች በመውጣት ሰልፍ አድርገው ነበር፡፡

በሰልፉም ህክምና፣የምግብና ሌሎች ድጋፎች እንዲደርጉላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

በርካቶቹ ከከባድ እስከ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ኪሮስ በግዚው ህክምና ቢያገኙ ሊድኑ የሚችሉ ነበሩ ብለዋል፡፡

ነገር ግን ህክምና ባለማግኘታቸው ለከፋ ችግር ሊዳረጉ ችለዋል ሲሉም ያክላሉ፡፡

የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር በስነልቦና፣በህክምና እና በምግብ እጦት ችግር ውስጥ የሚገኙትን ተጎጂዎች መፍትሄ ሊያፈላልግ ይገባዋል ሲሉም ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply