የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትረምፕ አማካሪ ስቲቭ ባነን እጃቸውን ሰጡ

https://gdb.voanews.com/C1F53A2D-0C05-4ED2-AB47-DFE466F84180_w800_h450.jpg

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የረጀም ጊዜ አጋርና አማካሪ የነበሩት ስቲቭ ባነን ዛሬ ሰኞ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ቀርበው መታሰራቸውን ሮይተርስ ዘገበ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤትን በመድፈር ሁለት ወንጀሎች የተፈላጊ የነበሩት ባነን፣ እጃቸውን ለመስጠት ወደ መጡበት የኤፍቢአይ ህንጻ ከመግባታችው በፊት በካሜራ ፊት “የባይደንን አስተዳደር እናስወግዳለን” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የዩናይትድስ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር ባላፈው ሳምንት፣ እኤአ ጥር 6 በምክር ቤቱ ህንጻ የተካሄደውን አመጽ የሚመረምረውን ምክር ቤት ኮሚቴ ጥሪ ባላመቀበል በ67 ዓመቱ ስቲቭባነን ላይክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ 

ባነን ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ቢያንስ ከ30 ቀናት እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስር ሊቀጡ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply