#የቀጠለው_የጀግንነት_ታሪክ_የበላይ_ዘለቀ_የልጅ_ልጅ_ፋኖ_ትዝታ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ)አሁን ባለው የሀገራችን ጦርነት በጀግንነት የተካፈለችው የበላይ ዘለቀ የልጅ ልጅ…

#የቀጠለው_የጀግንነት_ታሪክ_የበላይ_ዘለቀ_የልጅ_ልጅ_ፋኖ_ትዝታ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ)አሁን ባለው የሀገራችን ጦርነት በጀግንነት የተካፈለችው የበላይ ዘለቀ የልጅ ልጅ ልጅ የሆነችው የምስራቅ አማራ ፋኖ አባል ፋኖ ትዝታ ስማቸው ምህረቴ ካሰኝ በላይ ዘለቀ በራያ ግንባር ቆስላ አሁን ላይ ደሴ ሆስፒታል በጥሩ ጤንነት የህክምና ክትትል በማድረግ ትገኛለች የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት አባላት በቦታው ተገኝተው ሁሉንም ዋጋ የከፈሉ መስግነው ጠይቀዋል። ትግሉን የተቀላቀለችው ደቡብ ወሎ ምእራብ ወረዳ ተወልዳ ባደገችበት አካባቢ ወግዲ ነው ጀግናው አርበኛ በላይ ዘለቀም በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ /ቤተ አምሐራ/ የወሎን የንጉስ ሚካል ልጅ የአፄ ምኒልክ የልጅ ልጅ የሆነው እያሱ ሚካኤል አንጋች ባለሟል የነበረት ከአባታቸ…ው ከባሻ ዘለቀ ላቀውና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አስኔ ከጀግናወቹ እና ከአማራ ህዝብ መነሻ ቦታ ወሎ /ቤተ አምሐራ/ ክፍለ ሐገር #በአምሐራ_ሳይንት አውራጃ ወግዲ በጫቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሩ ጉጣ ከተባለው ቀበሌ በ1904 ዓ.ም ተወለዱ። 📜📒 /በ1983 ዓ.ም በፅሀፊ በአበራ ጀምበሬ ” አባ ኮስስቶር” መፅሁፍ ገፅ 8 ይገኛል/ አርበኛ በላይ ዘለቀ ገና ልጅ ሳሉ አባታቸው በሰው እጅ በመገደላቸው ምክንያት በእናታቸው እንክብካቤ ያለአባት አደጉ እድሜያቸው እየጨመረ ሲመጣም የአባታቸው ገዳይ ማን እንደሆነ በማወቅ ለመበቀል ገዳዩን ማፈላለግ ጀመሩ ጎጃም ለምጨን ተሻግረው የአባታቸውን ደም ለመበቀል ሲጠባበቁ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ በላይም ሀገርን የወረረውን የኢጣሊያን ጦር ለመውጋት ቆርጠው ተነሱ ብዙ ተከታዮችን በማፍራትም ወደ አርበኝነት ገቡ ጀግናው አርበኛ ከፋሺሽት ኢጣሊያ ጋር ባደሩጓቸው ተደጋጋሚ ውጊያዎች ታላላቅ ድሎችን አስመዘግበው በርካታ የኢጣሊያና የባንዳ ወታደሮችን በመማረክና በመግደል እንዲሁም የጠላት ጦር ካምፖችን በማቃጠል ታላላቅ ጀብዶችን ፈፀሙ፡፡ አሁንም ፋኖ ትዝታ ከምስራቅ አማራ ፋኖ ጋር በመሆን ሀገር አፍራሽ የሆነው የህውሃት ሀይልን ለማጥፋት ከፍተኛ ትግል አድርጋለች ቆስላለች በጣም የሚደንቀው አሁንም ተሽሎኝ ደግሜ ወደ ግንባር መግባት እፈልጋለሁ በማለት መልእክቷን አስተላልፋለች። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply