የቁጠባ ቤቶቹ ጉዳይ – አበበ ገላው

ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Ethiopian Latest News and Point of View 24/7

የጸረ ሙስና ኮሚሽን በህግ አግባብ ተቋቁሞ በጀት ከማባከን ውጪ እዚህ ግባ የሚባል ስራ ሰርቶ አያውቅም። በዘመነ ህወሃት እነ ኤፈርት፣ አዜብ መስፍን፣ አባዬ ጸሃዬ፣ ስብሃት ነጋና ቤተሰቡ፣ ብርሃነ ገብረክርስቶስ፣ እነ ስዩም መስፍን፣ ክንፈ ዳኘው…ባጠቃላይ ህወሃትና አጋሮቹ ህዝብና አገርን በጠራራ ጸሃይ ሲዘርፉ አላየሁም አልሰማሁም ብሎ ጋቢውን ተከናንቦ ተኝቶ ነበር። በእርግጥ አልፎ አልፎ ከእንቅልፍ እየባነነ ኮሚሽኑ አሳነባሪዎቹን ትቶ ትናንሾቹን አሳዎች ማለተም የበታች ሹማምንቶችና ደላሎችን ያሳስር ነበር። ይሄው አይጦቹን አባሮ የደለቡ የሙስና ሸለመጥማጦችን የመተው አባዜ አሁንም የለቀቀው አይመስልም። ህዝብ ተዘርፍኩ፣ ተበደልኩ እያለ ሲያነባ የእንባ ጠባቂ ኮሚሽኑም ቢሆን የማንንም እንባ አብሶ አያውቅም። መቼም ወያኔ ወገኛ ነበረች። ህዝብን እየዘረፈች የሙስና ኮሚሽን፣ ህዝብን ደም እያስነባች የእንባ ጠባቂ

The post የቁጠባ ቤቶቹ ጉዳይ – አበበ ገላው appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Ethiopian Latest News and Point of View 24/7.

The post የቁጠባ ቤቶቹ ጉዳይ – አበበ ገላው appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Ethiopian Latest News and Point of View 24/7.

Source: Link to the Post

Leave a Reply