የቃሊቲ_አዲስ_አሽከርካሪ_ብቃት_ማረጋገጫ_የመልካም_አስተዳደር_ችግሮችን_ለመፍታት ጥረት እያደረኩ ነዉ ብሏል፡፡ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ በፅሁፍና በነጻ የስልክ መስመር 7766 ጥቆማ…

የቃሊቲ_አዲስ_አሽከርካሪ_ብቃት_ማረጋገጫ_የመልካም_አስተዳደር_ችግሮችን_ለመፍታት ጥረት እያደረኩ ነዉ ብሏል፡፡

ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ በፅሁፍና በነጻ የስልክ መስመር 7766 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻልም ጠቁመዋል፡፡

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ (መንጃ ፍቃድ) ወደ 400 ተፈታኞች በማሳደግ ምሳ ሰዓትን ጨምሮ አገልግሎቱ ሳይቆረጥ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጾ ቀደም ሲል ተፈታኙ ፈተናውን ከተፈተነ በኃላ በCM የምዝገባ ቁጥር ውጤቱን ከሚያረጋግጥበት መንገድ በተጨማሪ በ 30 ደቂቃ ውስጥ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ውጤቱ እንዲደርሰው እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ከውጤት ጋር በተገናኘ ቅሬታ ካላው ቅሬታውን አቅርቦ በመስክ ላይ የነበረውን ሂደት በኮምፒውተር ተደግፎ እንዲመለከት እየተደረገ ሲሆን፤ በ15 ቀናት ውስጥ ለቀረበ 96 ቅሬታዎች በመመልከት አግባብነት ያለውና የሌለውን በመለየት ምላሽ መስጠት ተችሏል፡፡

የቃሊቲ አዲስ አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬው ደምሴ፣ አንድ ተፈታኝ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ከማሰልጠኛ ተቋማት የሚጠበቅበትን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት እኛ ዘንድ ከመጣ የተግባር ፈተናውን አስፈትነን በ30 ደቂቃ ውጤቱን አውቆ መንጃ ፍቃዱን ማግኘት እንደሚችል ለቴክኒክ ኮሚቴው ገልፀዋል፡፡

ይሁንና የጥቆማ መስጫዉ 7766 ነጻ የስልክ መስመር አገልግሎት ለማግኘት ሲደወል በተደጋጋሚ መስመሩ በመጨናነቁ አገልግሎት ለማግኘት እየተቸገሩ መሆኑን ተገልጋዮች ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply