የቅበት ከተማ ተፈናቃዮች ከታቦታቸው ጋራ ወደቀዬአቸው እንደተመለሱ ገለጹ

https://gdb.voanews.com/01000000-0a00-0242-7ea7-08dbdfbf916f_tv_w800_h450.jpg

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ፣ ከወራት በፊት የተፈናቀሉ 1ሺሕ200 የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ከትላንት በስቲያ ወደ ቀዬአቸው እንደተመለሱ ተናገሩ።

የክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይክ መሐመድ ኸሊልም፣ የተፈናቃዮቹ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተውላቸው ወደየቤታቸው እንደገቡ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስልጤ እና የሐዲያ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ፣ እርቅ ከወረደ በኋላ፣ ኹሉም ተፈናቃዮች ወደየመኖሪያ ቤቶቻቸው፣ ታቦታቱም ወደ ማረፊያ ደብራቸው እንደተመለሱ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply