
“የቅዱስ ሲኖዶሱን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አሰጥሮ በማቅረብ ሕዝብ በቀላሉ እንዲገባው አድርገሀል” በሚል የተከሰሰው ወጣት በእስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ ተከብሮ ቀድሞ ባስያዘው ዋስትና እንዲለቀቅ ተወስኖለታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው ወንድሙ ብርሃኑ ካባው ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርቦ በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ መወሰኑ አይዘነጋም። ውሳኔውን ተከትሎ የመፍቻ ትዕዛዝ ቢሰጠውም ፖሊስ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ጠይቆ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ቀርቦ ነበር ለውሳኔ በሚል ለየካቲት 3/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱነይታወቃል። ክሱም “የቅዱስ ሲኖዶሱን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አሰጥሮ በማቅረብ ህዝብ በቀላሉ እንዲገባዉ አድርገሀል” የሚል መሆኑ ብዙዎችን ያስገረመ ጉዳይ ሆኗል። የጋዜጠኛ ሙሉጌታ አምበርብር ዘገባ እንዳመለከተው ዛሬ የካቲት 3/2015 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት የእስር ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ተከብሮ ቀድሞ ባስያዘው ዋስትና እንዲጠናና እንዲለቀቅ ሲል ወስኗል።
Source: Link to the Post