የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በጣና ገዳም

ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ አብያተ ክርስትያናት፣ ገዳማትና አድባራት ይገኙባታል፡፡ እነሱን ተከትሎም በርካታ ታቦታት እና ንዋያተ ቅዱሳት አሏት፡፡እነዚህ ንብረቶቿ በገንዘብ የሚተመኑ አይደሉም፡፡ እጅግ ውድ መንፈሳዊ ቅርሶች ናቸው፡፡ኢትዮጵያ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የሐይማኖት ተከታዮች፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስትና ጳጳሳት ያሏት በክርስትናው አለም የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ጥንታዊት አገር ናት፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ምስጢራዊ ስፍራዎች ከሚባሉት ዋነኞቹ በታላቁ ጣና ሐይቅ ላይ የሚገኙት ገዳማት ናቸው፡፡እነዚህ ገዳማት ከቅድመ ክርስቶስ ዘመን ጀምሮ ያሉ የዕምነት ምኩራቦች እስከ አሁን ድረስ የሚነገርላቸው ቅርሶችን ይዟል፡፡በዛሬው ኢትዮጵያዊ ስንክሣራችንም የቅዱስ ገብርኤልን የንግስ በዓል ምክንያት አድርገን ጣና ላይ ወዳለው ክብሯን ገብርኤል ገዳም ውስጥ ቆይታ እናደርጋለን፡

አዘጋጅ እና አቅራቢ፡ ጥበቡ በለጠ

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply