የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሠራዊት ልጆች የመማሪያ ቁሳቁሶችን አበረከተ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሠራዊት ልጆች የመማሪያ ቁሳቁሶችን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሰራዊት ልጆች ደብተር፣ እስክርቢቶ እና እርሳሶችን ማበርከቱ ተገልጿል፡፡

የስፖርት ክለቡ ለሠራዊቱ ልጆች መማሪያ የሚሆን 50 ሺህ ደብተሮችን፣ 5 ሺህ እስክርቢቶና 5 ሺህ እርሳሶችን አበርክቷል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የስፖርት ማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ለመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ልዊጂ አስረክበዋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በቀጣይ ሳምንትም ወደ ማይካድራ በመጓዝ ለችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ወገናዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

The post የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሠራዊት ልጆች የመማሪያ ቁሳቁሶችን አበረከተ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply