የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን  ድጋፍ አደረገ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለአማራ ወጣቶች ማህበር አስረክቧል።

የስፖርት ክለቡ የሬዲዮ ክፍል ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ተወካይ አቶ ካሳሁን ደርቤ ሀገር መረጋጋት ስትጀምር ትውልድ መማር ስለሚቀጥል ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም 50 ሺህ ደብተሮች እና ከ30 ሺህ በላይ እስክርቢቶና ሌሎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለተቸገሩ ወገኖች እንዲደርስ በማሰብ ማበርከታቸውን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply