የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አለማድረጉን አስታወቀ።70 የኩላሊት ህመምተኞች የግድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ቢሆን…

https://cdn4.telesco.pe/file/fMF5FAw0ML7D8M8Ql4EtMWJh1VkIPqZh1WDuejHoLFRC0Cn2abcg1uCnz1ShHncu3IaHrYasg_2hMKnJwYPwZ6FQVG9ylVjfDiTjq0ENtXbbaXVKUD2sA3z5tsz4pcwqgxmrNI-wrqjClp7ju79aXF9337SgAkDyNodFRBlKpuCH-l_A9RnUdCGUHeHVna39wqXT9TYXQqYhWITIcrAzOqZdFWHzSenC4hjjCRH8SXYRL6A5s2hgkjYUURoME1FCSdxs8u22V50rBki5jdNqVaQ9Dz8H64fQ8CFiSAvcJInxcTAU8vwOMzzTWOUb4JSXM3CRl20YKWozah8z6wzjTQ.jpg

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አለማድረጉን አስታወቀ።

70 የኩላሊት ህመምተኞች የግድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ሆስፒታሉ ከዛሬ ነገ ስራ ይጀምራል እያሉ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ካደረገ 9 ወራት ማስቀጠሩ ተነግሯል።

ለዚህም ምክንያቱ የኮሮና ቫይረስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሆስፒታሉ የንቅለ ተከላ ማዕከል የነርስ አስተባባሪ የሆኑት ሲስተር ሀይማኖት ሀብተማርያም በኮሮና ምክንያት ጉዞዎች ስለተሰረዙ መደረግ ያለባቸው ምርመራዎችን ውጪ አገራት ልከን ማስመርመር አልቻልንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ህይወት ለማዳን የመጣን ሰው ህመም ሰጥተን አንሸኝም ብለን ነገሮች እስኪስተካከሉ እየጠበቅን ነው ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

የኮሮና ዳፋ ህሙማኑን በዲያሌሲስ እንዲቆዩ ያስገደዳቸው ሲሆን ይሄም ለከፍተኛ ወጪ ይዳርጋቸዋል ብለዋል ሲስተር ሀይማኖት፡፡

የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ በበኩላቸው በኮሮና ምክንያት ከባድ ጊዜን እያሳለፍን ነው ብለዋል፡፡

ከዚህም በላይ ደግሞ የመድሀኒት ዋጋ መጨመር ሌላው ፈተናችን ነው ብለውናል።

መቼ መፍትሄ ይሰጠዋል?ስንል ለጠየቅናቸው ጥያቄ
ሲስተር ሀይማኖት ሳምፕል ልከን የምናስመረምርበትን ሆስፒታል መቀየርን አማራጭ አድርገን አይተናል በቅርቡም ከውሳኔ ላይ እንደርሳለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply