You are currently viewing የቆሰሉ እና የደሙ ታላቅ ጀብዱ የፈፀመውን የአማራ ፋኖ በባህር ዳርን ያገለለ የባህር ዳር ከንቲባ  እውቅና እና ሽልማት⁉️ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 የአማራ ፋኖ በባህር ዳር የ…

የቆሰሉ እና የደሙ ታላቅ ጀብዱ የፈፀመውን የአማራ ፋኖ በባህር ዳርን ያገለለ የባህር ዳር ከንቲባ እውቅና እና ሽልማት⁉️ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 የአማራ ፋኖ በባህር ዳር የ…

የቆሰሉ እና የደሙ ታላቅ ጀብዱ የፈፀመውን የአማራ ፋኖ በባህር ዳርን ያገለለ የባህር ዳር ከንቲባ እውቅና እና ሽልማት⁉️ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 የአማራ ፋኖ በባህር ዳር የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልውና ጦርነት ለመመከት በጋሸና ግንባር በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አዝማችነት ፤ይህ ሲባል በከተማ አስተዳደሩ ኦርኔል ተሞልቶ እንዲሁም የትራስፓርት መኪና ከተማ አስተዳደሩ አቅርቦ የዘመተ የፋኖ ተቋም ነው ።በነበረው የህልውና ጦርነት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ሶስት(3) ጓዶቹን መስዕዋት ያደረገና አስራ ሰባት(17) ጓዶቹ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ ቁስለኛ ሆነውበት በአኩሪ ገድል የተመለሰ የፋኖ ተቋም ነው ።በጋሸና ለሰራው አኩሪ ጀብድ አሪቢት ምሸግ ላይ መታሰቢያ የተቀመጠበት የጀግና ስብስብ ነው ።ነገር ግን ካሳለፈነው ሳምንት ጀምሮ ይህ መንግስት ጓዶ…ቻችን በሃሰት ውንጀላ አፍኖ አስሯል እንዲሁም በርካቶችን ለማፈን በአሁኑ ወቅትም እንቅስቃሴ ላይ ናቸው። ይህ ሆኖ እያለ በዛሬው ዕለት ማለትም በ30/10/2014 ዓ.ም የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባው ዶ/ር ድረስ ሳህሉ እና አመራሩ በህልውና ዘመቻው የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትና ድርጅቶች[[ለነዚህ ተቋማትና ግለሰቦች የሚደረገው እውቅና ላይ ምንም አይነት ችግር የለብንም❗️]] እንዲሁም የህይወት መስዕዋትነት ለከፈሉ ፤ለቆሰሉ ግለሰቦች ያደረገው እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር ፍፁም ክህደት የተሞላበት ፤የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ያገለለ እንደሆነ ለመላው የከተማችን ህዝብ ማሳወቅ እንወዳለን ። የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ጀግና አባላት በትክክል እውቅና የሚገባው ስብስብ ነበር ።በትክክልም ለከፈለው መስዕዋትነት ህዝቡ ሙሉ እውቅና የቸረው ነው ።መታወቅ ያለበት መላ አባላቱ ከመንግስት የሚመጣን እውቅና ፈልጎ አልነበረም ወደ ጋሸና የዘመተው ፤ መሰዕዋትነት የከፈለው ፣የቆሰለው እና የደማው ለማንነቱ ፣ለደረሰብን ወረራ እና ለከበረው የአማራ ህዝብ ብሎ ነው ። የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በቀደምት አባቶቻችን የፋኖነት ታላቅ መንፈስ ነው ዋጋ የከፈለነው ወደ ፊትም የምንከፍለው ።በአንድ ወቅት ጀግናው በላይ ዘለቀ ንጉሠ ነገስቱ ፊት ቀርቦ ምን ላድርግልህ ተብሎ ሲጠየቅ ⁉️የመለሰው እንዲህ ነበር <<እናቴ አንዴ በላይ ብላኛለች ምንም ሽልማት አልፈልግም ነበር ያለው‼️>> እኛም ጀግና የሚለካው አንዴ ነው ፤አንድ ጊዜ ፋኖ የሚለውን የከበረ ፣ታላቅ እና አኩሪ ስም ይዘናልና ሽልማታችን ነፃነታችን ፤የአማራ ፋኖ የሚለው ስማችን ነው ። ነገር ግን በዛሬው ዕለት የተካሄደው የእውቅና ፕሮግራም ፍፁም ክህደት የተሞላበት የቆሰሉና የደሙ ፤ታላቅ ጀብዱ ፈፅመው በህይወት የተመለሱ ጓዶቻችን የዘነጋ አሳፋሪ፣ አስነዋሪ እና ከፋፋይ የሆነ የከተማ አስተዳደሩ ተግባር ግን መላው የከተማችን ህዝብ እውቅና እንዲኖረው እያልን ፤ ይህንን ከፋፋይ አካሄድ በፅኑ መታገልና ማውገዝ እንዳለብን የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ጥሪውን ያስተላልፋል ። ፋኖነት ከቀደምት አባቶቻችን በውርስ የተቀበለነው ፤የተሸለምነው የክብር ፤የነፃነት እና የአይበገሬነት መታወቂያችን ፥ሽልማታችን ነው ‼️ © የአማራ ፋኖ በባህርዳር

Source: Link to the Post

Leave a Reply