#የቋራ አካባቢ ፋኖዎቹ አባይ ዳር በሚባል ቀበሌ ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ ተብለው መታፈናቸው ተሰማ! ሕዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የክተት ጥሪውን ተቀብለው በግንባር…

#የቋራ አካባቢ ፋኖዎቹ አባይ ዳር በሚባል ቀበሌ ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ ተብለው መታፈናቸው ተሰማ! ሕዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የክተት ጥሪውን ተቀብለው በግንባር ከጠላት ጋር ተፋልመው ድል አድርገው የተመለሱ የፋኖ አባላት ላይ ህዳር 1ቀን 2015 ዓ/ም ሆን ብሎ አባይዳር በሚባል ቀበሌ ቋራ ውስጥ በብልፅግና ተልዕኮ አማራን ለመከፋፈል በሚሠሩ ባዳወች ተኩስ ተከፍቶባቸው 3 የፋኖ አባላት ህይወት ሲያልፍ ፤ 2 የፋኖ አባላት ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የገለፁት ምንጮቻችን የተፈጠረውን ችግር ለመፈታት በሚል በቀን18/3/2015 ዓ/ም ፋኖዎችን ስብሰባ ከጠሩ በኃላ ሰውረዋቸዋል ብለዋል። እነዚህ ፋኖወች ከታገቱበት ቀን ጀምረው እስካሁን ቤተሰቦቻቸውም ይሁን የቅርብ ጓደኞቻቸው እንዳይጠይቃቸው በማድረግ ቋራ በሚገኘው የልዩ ሀይል ካምፕ ታግተው እንደሚገኙ ምንጮች አረጋግጠዋል ። ብልፅግና ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ናቸው የሚላቸውንእና አማራን በማዳከም ሴራ ሊወድቁለት ያልቻሉትን የቁርጥ ቀን ልጆች በባትሪ እየፈለገ በማሰር እና በማሳደድ ላይ ይገኛል ምንጮቻችን ከአሻራ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ። አሁላይ ሁሉም አማራ በሚባል ደረጃ በሆዳሞች የሚሰራብንን የመከፋፈል ሴራ ስለተረዳን ሁሉም የአማራ ፋኖ አስተሳሰብም ይሁን ዓለማ አንድ ዓማራ ስለሆነ የብልፅግና ካድሬዎች እኛን ለመከፋፈል ያሰቡትና የሸረቡት ሴራ ትርፉ ድካም ነው የሚሆንባቸው ሲሉ ጨምረዋል። ፋኖ በሰላም ጊዜ አራሽ ገበሬ ነው። የሃገር ህልውና አደጋ ላይ በወደቀ ጊዜ ደግሞ የግል ጉዳዩን ከሃገር አይበልጥም ብሎ ወደጎን በመተው ግባር ዘምቶ ጠላትን የሚፋለም ጀግና ነው ሲሉ አክለዋል። ካሁን በፊት በክተት አዋጅ አገር ያተረፉ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ደግሞ አንፃራዊ ሠላም አለ ። ሠብል አምርተው ከርመው ሰብል በሚሠበስቡበት ሠዓት አማራን በኢኮኖሚም ይሁን በሞራል ለመጉዳት የሚደረገውን ሙከራ በማምረር የአካባቢው ህብረተሠብ እሮሮውን እያሠማ እንደሚገኝ የአሻራ ሚድያ ምንጮች ጨምረው ተናግረዋል። ፎቶ:- ከፋይል ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply