የበላይ አብ ሞተርስ ባለቤት ናቸው የተባሉ አቶ ጌትነት አበበ በህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ይዞ በመገኘት ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

የበላይ አብ ሞተርስ ባለቤት ናቸው የተባሉ አቶ ጌትነት አበበ በህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ይዞ በመገኘት ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የበላይ አብ ሞተርስ ባለቤት ናቸው የተባሉ አቶ ጌትነት አበበ በህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ይዞ በመገኘት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀረቡ፡፡
መርማሪ ፖሊስ ተጠተርጣሪው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በሚገኘው ድርጅታቸው ውስጥ አግኝቻለው ያለው አንድ ክላሽ እና 30 ጥይት ፍቃድ እንዳለው ገልጿል፡፡
አንድ ኮርት ሽጉጥ በአባታቸው ስም የተመዘገበ መሆኑን ተጠርጣሪው የገለፁ ቢሆንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ግን ፍቃዱን አለማግኘቱን ገልፆ ሌላ አንድ ምንሽር ከ95 ጥይት ጋር እና 240 የክላሽ ጥይቶችም ፍቃድ የሌላቸው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል፡፡
በተጨማሪም ፖሊስ በጉምሩክ ኮሚሽን ያልተመዘገበ 71 ሺህ 625 የአሜሪካ ዶላር በቤታቸው አግኝቻለው ያለ ሲሆን በድርጅታቸው ውስጥ አንድ ታርጋ የሌለው መኪና አግኝቻለው ሲል ለችሎቱ ገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎም ዶላሩን የመለወጥ እና የመሸጥ ፍቃድ እንዳላቸው እያጣራው ነው ብሏል መርማሪ ፖሊስ፡፡
የተጠርጣሪው ጠበቃም መኪናው ድርጅታቸው ውስጥ ለስራ የመጣና ባለቤት ያለው ነው ሲል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
መርማሪ ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የጠየቀውን 14 ቀንም ተቃውመዋል፡፡
የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም የተጠርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው ውድቅ በማድረግ ለተጨማሪ ምርመራ 12 ቀን ለፖሊስ ፈቅዷል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የበላይ አብ ሞተርስ ባለቤት ናቸው የተባሉ አቶ ጌትነት አበበ በህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ይዞ በመገኘት ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply