የበረሀ አንበጣ መረርሺኝን ለመከላከል ጠንካራ ስራ አንዲሰራ ተጠየቀ።

የግብርና አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የግብርና ሚኒስተር የበረሀ እንበጣ ወረርሺኝ የመከላከልና የመቆጣጠር ዘለቄታዊ መፍትሄ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴዉ በ2013 በጀት አመት በ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና በአካል በተደረጉ የመስክ ምልከታዎች በግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት እቅድ አፈጻጸም የታዩ ጥንካሬዎችን፣ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸውን ጉዳዮችን እና ከተቋማት አቅም በላይ የሆኑና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን እገዛና የሌሎችን ተቋማትን ቅንጅትና ትብብር የሚፈልጉ ችግሮችን በማካተት ለውይይት መነሻ የሚሆን ሀሳብ አቅርቧል፡፡

ቋሚ ኮሚቴዉ ገመገምኳቸዉ ያለዉን ችግሮች ጠቅሶ በሩብ አመቱ ኤክስፖርት የሚደረጉ 80 ሺ የዳልጋ ከብቶችን የጤና ምርመራ በማድረግ በእቅዱ የጠቀመጠ ቢሆንም ከእቅዱ 18 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ አፈጻጸም የታየበት ነዉ ያለ ሲሆን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፤ ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ እና በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ የበረሀ እንበጣ መንጋ ወረራን የመከላከል እና የመቆጣጠር ዘለቄታዊ መፍትሄ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም በግምገማዉ አመላክቷል፡፡

ተቋማቱ የተሰጣቸዉን ተግባር እና ሃለፊነት እንዳይተገብሩ ችግር የሆነባቸዉን እና በቋሚ ኮሚቴዉ እና በሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች መመለስ የሚገባቸዉ ጉዳዮችም ቀርበዋል በተለይም የትራንሰፖርት የህግ እና ደንብ ጉዳዮችን ባፋጣኝ ማጽደቅ ተጠቃሾቹ ናቸዉ፡፡

የበረሀ እንበጣን በሚመለከትም በግብርና ሚኒስተር ብቻ የመከላከል እና መቆጣጠር ስራዉን አዳጋች ስለሚያደርገዉ የሚመለከታቸዉ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

**************************************************************************

ዘጋቢ፡ ቤዛዊት ግርማ

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply