የበረኸት ወረዳ ፋኖ አደረጃጀት ያሰለጠናቸውን አባላት አስመረቀ በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ፋኖ አደረጃጀት ከ200 በላይ ወታደራዊ ስልጠና ያጠናቀቁ የፋኖ አባላትን አስመረቀ፡፡ አማራ…

የበረኸት ወረዳ ፋኖ አደረጃጀት ያሰለጠናቸውን አባላት አስመረቀ በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ፋኖ አደረጃጀት ከ200 በላይ ወታደራዊ ስልጠና ያጠናቀቁ የፋኖ አባላትን አስመረቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ የበረኸት ወረዳ ፋኖ አደረጃጀት ያሰለጠናቸውን አባላት አስመረቀ በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ፋኖ አደረጃጀት ከ200 በላይ ወታደራዊ ስልጠና ያጠናቀቁ የፋኖ አባላትን አስመርቋል። በእለቱ የአሳገርት፣ የሀገረ ማርያም፣ የደብረ ብርሃን፣ የአረርቲና ምንጃር የፋኖ አባላት ታድመዋል፡፡ ፕሮግራሙን የከፈቱት የበረኸት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ከበረ ይልማ ፊት ለፊት በመፋለም ለዚህ እለት ላደረሱን የፋኖ አባላት፣ መከላኪያ ሰራዊት፣ሚኒሻና ልዩ ሀይል የከበረ ሰላምታ አቅርበዋል። አንድነታችንን በማጠናከርና በመደራጀት ለጠላት የማትደፈር ሀገር መገንባት አለብን ብለዋል፡፡ አክለውም አስቸጋሪ ጉዞ አድርገው ፍቅር በሆነችው ወረዳ ላይ ለተገኙ እንግዶች የተሰማቸው ኩራትና ደስታ ገልፀዋል፡፡ የሸዋ አማራ ፋኖ ሊቀ መንበር ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ በበኩላቸው በረኸት ወረዳ የጀግኖች ሀገር መሆኗን አብራርተዋል፡፡ ለነጮች አንገዛም በማለታቸው ከ300 በላይ የወረዳዋ አርበኞችን ጣሊያን መረሸኑንም አብራርተዋል፡፡ አክለውም ፋኖ ማለት ለህዝብ የሚሞት ከህዝብ በፊት በመቅደም በህዝብ ላይ የሚደርስ መከራ፣ሀዘንና ሰቆቃን ለማስቀረት የሚታገል የጀግና ስብስብ ማለት እንደሆነ አብራርተዋል። ፋኖ ከሺ አመታት በፊት ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በሌለበት ሰዓት በአርበኝነት ሀገሩን ያስከበረ መሆኑንም መሰክረዋል፡፡ በመጨረሻም ተፈጥሮአዊ የሆነውን ራስን የመከላከል መብት ለማስከበር ፋኖን መቀላቀልና መደራጀት እንደሚያስፈልግ ተገልጧል። የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

Source: Link to the Post

Leave a Reply