የቡድን 20 አባል አገሮች ጉባኤ ተጀመረ

https://gdb.voanews.com/EF5DAF33-EAD3-467F-8839-B6A57AFBBA7F_w800_h450.jpg

የበለጸጉ አገራት መሪዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝና የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ፣ በሚያሳስቧቸው የጋራ ጉዳዮች ለመነጋገር፣ ዛሬ ቅዳሜ ጣልያን ሮም ውስጥ በተመጀመረው የቡድን 20 አባል አገራት ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በሮም የኮንቬንሽ ሴንተር በሚካሄደው ስብሰባ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማርዮ ድራጊ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን ጨምሮ፣ ሌሎች መሪዎችን የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል በሚፈቅደው መሠረት ተቀብለዋል፡፡

መሪዎቹ ከሁለት ዓመት በኋላ በአካል ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡

በስብሰባው ላይ የቻይናው ፕሬዚዳን ጂ ፒንግ፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦርባዶር በአካል ያልተገኙ ሲሆን ስብሰባውን በድረገጽ እንደሚሳተፉ ተገልጧል፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply