የቢሻንጉል ጉምዝ ምክርቤት ነገ በሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ የከፍተኛ አመራሮች  ያለመከሰስ መብት እንደሚነሳ ተገለፀ፡፡ (አሻራ ታህሳስ19፣ 2013ዓም)  በሁለት ወራት ውስጥ ብቻ ከአንድ…

የቢሻንጉል ጉምዝ ምክርቤት ነገ በሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ የከፍተኛ አመራሮች ያለመከሰስ መብት እንደሚነሳ ተገለፀ፡፡ (አሻራ ታህሳስ19፣ 2013ዓም) በሁለት ወራት ውስጥ ብቻ ከአንድ…

የቢሻንጉል ጉምዝ ምክርቤት ነገ በሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ የከፍተኛ አመራሮች ያለመከሰስ መብት እንደሚነሳ ተገለፀ፡፡ (አሻራ ታህሳስ19፣ 2013ዓም) በሁለት ወራት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሺ ንፅሃን በላይ በግፍ የታረዱበት የመተከሉ ጉዳይ በመንግስት መዋቅር እንደሚመራ ተደርሶበታል፡፡ የበላይ አመራሮች ከለላ በመስጠት ከ80 ሺ በላይ ንፅሃንን ተፈናቅለዋል፡፡ ንብረት ወድሟል፡፡… የቢሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ታደለ ተረፈ ለኢሳት እንዳረጋገጡት በነገው ስብሰባ በወንጀል የተጠረጠሩት ያለመከሰስ መብታቸው ይነሳል፡፡ ክስም ይመሰረትባቸዋል፡፡ የመተከሉ ጉዳይ ዛሬም አስተማማኝ ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ አሻራ ሰምቷል፡፡ የመወከል፣ ተቋም እና ስራዓት ማሻሻል ግን ዘላቂ መፍትሄዎች እንደሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ ከመተከል ታጣቂዎች ጀርባ ከመንግሥት ባለስልጣናት ባለፈ፣ የውጭ ሀገራት ጣልቃገብነትም እንዳለበት ይታወቃል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply