የቢሻንጉል ጉምዝ ምክርቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ፡፡ አስቸኳይ አዋጁ የመተከሉ ጉዳይ እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 19፣ 2013ዓ.ም) ከመተከል ህዝብ 40% የተፈናቀለበት እና…

የቢሻንጉል ጉምዝ ምክርቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ፡፡ አስቸኳይ አዋጁ የመተከሉ ጉዳይ እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 19፣ 2013ዓ.ም) ከመተከል ህዝብ 40% የተፈናቀለበት እና የመንግስት መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ ስራ ያቆመበት የቢሻንጉል ጉምዝ አስተዳድር የሚታሰሩ አመራሮችን የሚለይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ክልል አመራሮችም የሚወገዙበት እንደሚሆን ውስጥ አዋቂዎች ለአሻራ ተናግረዋል፡፡ የችግሩ ምንጭ የአማራ የመስፋፋት ዝንባሌ ነው የሚል ሀሳብ እንዲሰጥ በተረኛ ነኝ ባይ ብልፅግናዎች እየዳበረ ነው፡፡ የውሸት ትርክቱ ዛሬም ገና አልቆመም፡፡ በሌላ በኩል በወለጋ ሁሩ ጉድሩ ዞን ጃርቲጃርደጋ ወረዳ ከ30 በላይ አማራዎች ታርደው አድረዋል፡፡ የሚደርስ የፀጥታ አካልም ጠፍቷል፡፡ ሞት እየረከሰ ነው፡፡… የአማራ ብልፅግና በወሬ የተጠመደ ሲሆን፣ ተግባር ነጥፎበታል፡፡ ዶክተር አለሙ ስሜ ማንም ባለስልጣን ከብልፅግና ፈቃድ ውጭ ቃለመጠይቅ ማድረግም ሆነ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መፃፍ የለበትም ካሉ በኃሏ ባለስልጣናት በሙሉ ጭር ያለች ዶሮ መስለዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply