የቢጂአይ ንብረቶችና የባንክ አካዉቶች እንዳይንቀሳቀሱ በፍርድቤት መታገዱ ተሰማ፡፡

ፐርፐዝ ብላክ የቢጂአይ ኢትዮጵያ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችና የባንክን አካዉንቶች እንዳይንቀሳቀሱ እና ገንዘብ እንዳይወረስብኝ በሚል ያቀረበዉ የእግድ ጥያቄ በፍርድቤት ተቀባይነት አግኝቷል።

ፐርፐዝ ብላክ በጠበቆቹ አማካኝነት የካቲት 27 ቀን 2016 ዓም በተፃፈ አቤቱታ የክስ ዝግጅት አጠናቅቆ የብር 1, 519,000000 ክስ እስከማቀርብ ድረስ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ጥሬ ገንዘብ እንዳይሰውርብኝ እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረቱ እንዳይሸጥብኝ አስቸኳይ እግድ ይሰጥልን በሚል በፍትሃ ብሔር እና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት ዉሳኔ መስጠቱ መገለጹን ካፒታል አስነብቧል።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የካቲት 28፤2016 በከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃ ብሄር ምድብ ችሎት የቢጂአይ ኢትዮጵያ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችና የባንክ አካውንቶች እንዳይንቀሳቀሱና ገንዘብ እንዳይሰወርብኝ በሚል ባቀረበው የእግድ ጥያቄ መሰረት ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ተቀብሎ የባንክ አካውንትና የማይንቀሳቀሱ የቢጂአይ ኢትዮጵያ ንብረቶች እንዳይሸጡና እንዳይለወጡ እግድ መጣሉን ለማወቅ ተችሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply