የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ መቋረጡ ተገለጸ፡፡ የቢጂአይን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭን አስመልክቶ በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/MFNHPVdwPwwQ1cu9rF3MMKKulyujEBDaXmNeNOmvDn7DFQBe4bfy_2tZsDbG3ogIUi2waCjSe6l9IU-37Te7AGK8in4NgQK4rnVEAr4p7XAsLGy2TXJsj-qTeef31MHkbdt-k2rxGmpeORdQg4Rpa8lVq1cVZb0rf_Ne3VKgkk_0FukopTy-5YgrI7pxVKGhzkgEiB7LUdsZEGYmATQlsXxYvHVpHfopVl9BLu7toRRmRY-VdwcyuTgZZnhibL4keqafFt3QINFB8TpxdEg937smLOumM6pJheY_doNYUFSV42LL7E4EmgKQRcuYrALYDvKO7dCD6wLE1HDctwyQ1g.jpg

የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ መቋረጡ ተገለጸ፡፡

የቢጂአይን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭን አስመልክቶ በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር የሽያጭ ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡ ታውቋል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የሽያጭ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንዲኖር እና የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ እውን እንዲሆን ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም፤ በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ትሬዲንግ አ/ማ በኩል ግብይቱን ለማጠናቀቅ እና የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ምክንያት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደቱን ለማቋረጥ ተገደናል ብሏል ቢ ጂ አይ።

ስለዚህም በተዋዋይ ወገኖቹ ቀድም ሲል በተፈረመው የቀብድ ውል ውስጥ በተገለጹት ድንጋጌዎች መሠረት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጩ በይፋ ተቋርጧል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የ2028 ራዕዩን እውን ለማድረግ እና የምርት አቅሙን በእጥፍ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጾ፣ ከዋና መስርያ ቤቱ ሽያጭ ድርድር ጋር በተገናኘ በዚህ ወቅት ምንም አይነት ተጨማሪ አስተያየት የማይሰጥ መሆኑንም በላከልን መግለጫ አመላክቷል፡፡

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሰጠው መግለጫ 1 ቢሊዮን ብር ቅድሚያ ክፍያ መፈጸሙን መግለጹ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply