You are currently viewing የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የአፍሪካ ቱሪዝም የዓመቱ ጀግና ሴት ተብለው ተመረጡ

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የአፍሪካ ቱሪዝም የዓመቱ ጀግና ሴት ተብለው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የፈረንጆቹ 2019 ምርጥ የአፍሪካ ቱሪዝም መሪ ሆነው ተመረጡ፡፡

ምርጫውን ይፋ ያደረገው በጋና የሚገኘው ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን የተሰኘው ድርጅት ነው ተብሏል፡፡

ሽልማቱ ከአስር ቀናት በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

ዶክተር ሂሩት በቱሪዝም፣ በሆቴልና መስተንግዶ በአጠቃላይ በዘርፉ ላይ ለተሰማሩ እና ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራኞተችና አመራር በሙሉ እውቅናው የእናንተ ነውና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

“እጅ ለእጅ ተያይዘን ከሰራን ገና ሩቅ እንጓዛለን በማለትም” በማህበራዊ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

The post የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የአፍሪካ ቱሪዝም የዓመቱ ጀግና ሴት ተብለው ተመረጡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply