የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ የባህርዳር ከተማ ኤርፖርት ስያሜ እንዲቀየር ወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባ…

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ የባህርዳር ከተማ ኤርፖርት ስያሜ እንዲቀየር ወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባለፉት አመታት “የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት ” ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ በህብረተሰቡ ፍላጎት ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ በዛሬው ዕለት ታህሳስ 09/2013 የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ “የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት” ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል ። ይህ ስያሜ ከ1983 ዓ.ም በፊትም ይጠራበት እንደነበር ያስታወሰው የከንቲባ ኮሚቴው የህዝቡን ፍላግትና የከተማውን ወካይ ስያሜ በመምረጥ ስሙ እንዲቀየር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል። ተቋርጦ የነበረውም የአውሮፕላን ትራንስፖርት ከነገ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎት እንደሚጀምር ነው አስተባባሪ ኮሚቴው የገለፀው። ምንጭ_የባህርዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤትን ጠቅሶ አማራ ብልፅግና በገጹ እንዳሰፈረው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply