የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ተገደሉ::የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መ…

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ተገደሉ::

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ የነሩት ኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸዉ አልፏል።

ኮማንደሩ በፀጥታ በማስከበር ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት አካባቢ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመትተዉ ለህዝብና ለሀገር ሲሰሩ መስዕዋት ሆነዋል ሲል የክልልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

ፖሊስ ኮሚሽኑ በኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ሀዘን ገልጾ ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ረፋድ መፈፀሙን እስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply