
የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች ላይ የተሰነዘረው የቦንብ ጥቃት በጣም አሳፋሪ እና ነውርም ነው ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህርዳር (አወማ) አስታወቀ። ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በንፁሃን ዜጎች ፣ ኳስ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ የለም ።እንደዚህ አይነት ነውረኛ ተግባር በመፈፀም የአማራ ህዝብ ለመከፋፋል የሚደረግ እንቅስቃሴ ተሞክሮ የከሸፈ ያለፈበት ተግባር ነው ። በፈተና ወቅት ህዝባችን ከምንጊዜውም በላይ አንድነቱን አስጠብቆ ይዘልቃል ። የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ጉዳት በደረሰባችሁ ወንድም ፣እህቶቻችን ቁስላችሁ በተሎ ይሽር ዘንድ ያለውን ወገናዊ ምኞቱን ይገልፃል ። ድል ለጣናው ሞገድ‼️ ድል ለአማራ ህዝብ‼️ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post