የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ”የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት” ተብሎ እንዲጠራ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አመታት “የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት ” ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ”የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት” ተብሎ እንዲጠራ ተወሰነ፡፡
ባለፉት አመታት “የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት ” ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ በህብረተሰቡ ፍላጎት ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ ዛሬ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ነው “የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት” ተብሎ እንዲጠራ የተወሰነው ።
ይህ ስያሜ ከ1983 ዓ.ም በፊትም ይጠራበት እንደነበር ያስታወሰው የከንቲባ ኮሚቴው የህዝቡን ፍላግትና የከተማውን ወካይ ስያሜ በመምረጥ ስሙ እንዲቀየር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።
ተቋርጦ የነበረውም የበረራ አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎቱን እንደሚጀምር አስተባባሪ ኮሚቴው መግለፁን ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ”የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት” ተብሎ እንዲጠራ ተወሰነ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply