የባህር ዳር ነዋሪዎች በግፍ ለታሰሩ ፋኖዎችና ወጣቶች ያላቸውን አክብሮት በተግባር እያሳዩ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

የባህር ዳር ነዋሪዎች በግፍ ለታሰሩ ፋኖዎችና ወጣቶች ያላቸውን አክብሮት በተግባር እያሳዩ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ከተማ በግፍ ለታሰሩ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮችና ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች በመምጣት በከተማዋ ተሰብስበው ስለአብሮነት ሲመክሩ ለታፈኑ 14 የአማራ ፋኖዎች ህዝቡ አክብሮቱንና አብሮነቱን በተግባር እየገለጸላቸው ይገኛል። በተለይም ሀምሌ 8/2014 ከጠዋት ጀምሮ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አዳራሽ እና በዙሪያው የተገኙ በርካታ የባህር ዳር ፋኖዎችና ሌሎች ንቁ ወጣቶች በግፍ እስር ላይ የሚገኙትን ፋኖዎችን አበረታተዋል። ገብተው ችሎቱንም በመታደም ከጎናቸው እንደሆኑ እየገለጹ ነው። ከጠዋት የጀመረው ችሎትም ከሰዓት በኋላም እንደሚቀጥል ተሰምቷል። ፎቶ_ያሬድ አላዩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply