
የባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው ወጣቶች በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት በሚከናወነው በእነ አሸናፊ አካሉ ችሎት በመገኘት አማራዊ አጋርነትና ወንድማዊነትን እንዲያሳዩ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ታጋይ አሸናፊ አካሉ ፣የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ፍትህአለው አሰፋ እና የአርበኛ ዘመነ ካሴ ሾፌር ፋኖ ዘሪሁን የካቲት 14/2015 ጠዋት በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ይቀርባሉ። ታጋይ አሸናፊ አካሉ ፣የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ፍትህአለው አሰፋ እና የአርበኛ ዘመነ ካሴ ሾፌር ፋኖ ዘሪሁን የካቲት 14/2015 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ባህርዳር ከተማ እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ይቀርባሉ ብሏል የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር። በመሆኑም ለግፉአን አለኝታ የሆናችሁ የባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው ወጣቶች በችሎት በመገኘት አማራዊ አጋርነታችን ፣ወንድማዊነትን እንገልፅ ዘንድ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ቅርንጫፍ የተከበረ ጥሪውን ያስተላልፋል። በማሰር እና በማዋከብ የሚቆም ፣የተጀመረ የአማራ ትግል ፈፅሞ የለም። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል!
Source: Link to the Post