የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዚምቧቤ አከበረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ…

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዚምቧቤ አከበረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ የምስረታ በዓሉን በዚምቧቤ ሀራሬ ከታህሳስ 12-16/ 2022 ማክበሩን አስታውቋል። ዩኒቨርስቲው RUFORUM 2022 በተሰኘው ስብሰባ ከተሳተፉ 147 የአፍሪካ አህጉር ዩኒቨርስቲዎች አንዱ ነው። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ የተመራ የልኡካን ቡድን ነው የምስረታ በዓሉን በባነር አውደ ርዕይ ያከበረው። ስለባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ታሪክ በጨረፍታ እንዲመለከቱ አስችሏቸዋል ካለፉት ጊዜያት ጀምሮ እስከ አሁን ያደረጋቸውን ተግባራት የሚያሳይ ባነር አዘጋጅተው አቅርበዋል። በበአሉ ላይ ዩንቨርስቲው በምርምር እና ኢኖቬሽን ስራዎች ላይ ያከናወናቸውን ድሎች በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ እንደ አንድ ታዋቂ ዩንቨርስቲ አሳይቷል። ኤግዚቢሽኑ ዩኒቨርሲቲው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያለው ዩኒቨርሲቲ የመሆን ራዕዩን በሂደት እንዲያሳካ፣ አዳዲስ ሽርክናዎችን፣ ኔትወርኮችን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን እንዲመረምር ዕድል ሰጥቶታል ተብሏል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተመዝግበው ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply