You are currently viewing የባልደረስ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ በቁጥጥር ስር ዋለ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ መንግስታዊ አፋኝ ቡድን “ህግ ማስከበር”…

የባልደረስ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ በቁጥጥር ስር ዋለ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስታዊ አፋኝ ቡድን “ህግ ማስከበር”…

የባልደረስ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ በቁጥጥር ስር ዋለ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስታዊ አፋኝ ቡድን “ህግ ማስከበር” በሚል የሽፋን ቃል አዲስ አበባን ጨምሮ በተለይም በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች አፈናውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። በአዲስ አበባ በተለይም የባልደራስ አባላትን ጨምሮ ጋዜጠኞች የዚህ መንግስታዊ አፈና በቀዳሚነት ተጠቂዎች ሆነዋል። በየጊዜው አመራሮችና አባላቱ በግፍ እየታሰሩበት የሚገኘው ባልደራስ ግንቦት 17/2014 ናትናኤል ያለምዘውድ የተባለ አባሉ እንደታሰረበት አስታውቋል። ከአድዋ እና ከካራማራ የድል በዓላት አከባበር ጋር በተያያዘ ከታሰሩት በርካታ የባልደራስ አባላትና የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል አንዱ የነበረው ናትናኤል ያለም ዘውዱ በድጋሜ በፖሊስ ታስሮ በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መግባቱ ታውቋል። በእለቱ አብሮት የነበረው ጋዜጠኛ ይድነቃቸው ከበደ የሚከተለውን አጋርቷል:_ የናቲ እስር እና የሆነው ነገር… ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲሱ ገበያ ምሳ አዘን እንደቀረበ ፤ የቀረበው ምግብ እንኳን ሳንጎርስ ፤ አጠገባችን አራት ሰዎች መጥተው “ናቲ፤ አንዴ ወደ ውጪ እንውጣ። ልናናግርህ እንፈልጋለን ” አሉት ፤ በዚህን ጊዜ እኔ እና ናቲ ተያየን…..፤ ይህን ጊዜ የክትትሉ ዋና አስተባባሪ የሆነው ” ይድኔ ሰላም ነው። ለጥያቄ ነው ችግር የለም።… ናቲ ተነስ” በማለት እሱን ከፊት አስቀድመው ከሆቴል ይዘውት ወጡ። በሆቴል ውስጥ የነበሩ አስተናጋጆች እና የተወሰኑ የሆቴሉ ተጠቃሚዎች፤ እኛ የነበርንበት የምግብ ጠረጴዛ አካባቢ እየሆነ ባለው ነገር ዓይናቸውን እና ጆሮቸውን ጥለው ይከታተሉን ጀመር። በሆነው ነገር ግራ ገብቷቸዋል! ወዲያውኑ ይዘውት በመጡት መኪና ውስጥ ናቲን ካስገቡት በኋላ ዋና አስተባባሪው ወደ እኔ በመምጣት ” ይድኔ ፖሊሶች ነን!” በማለት ከኪሱ መታወቂያውን አውጥቶ እያሳየኝ፤ “አንተም ወደ መኪናው ውስጥ ግባ። ለተወሰነ ጥያቄ ነው የምንፈልጋችሁ ትመለሳላችሁ።” በማለት መኪና ውስጥ እንድገባ በሩን ከፍቶ አመላከተኝ። እኔም በተከፈተው መኪና ወደ ውስጥ እየገባሁ እንዳለ ፤ አንደኛው ፖሊስ “መኪናው እዚህ መቆሙ ጥሩ አይደለም ። ሊዘረፍ ወይም ንብረት ሊሰረቅ ይችላል። ቁልፉን አምጡ!። ማን ጋር ነው?” አለ። “እዛው ምግብ ቤት ጠረጴዛ ላይ ነው” አልነው ። ዋናው አስተባባሪ ወደ ምግብ ቤቱ ወዲያውኑ ቁልፉን ለማምጣት ሄደ…፤ ብዙም ሳይቆይ ዋናው አስተባባሪ ወደ ነበርንበት መኪና በመምጣት “ቁልፉ የለም ሆቴል ውስጥ።” አለ። ይህን ጊዜ እኔም፣ ናቲም ወደ ኪሳችን ገባን። የመኪናው ቁልፍ እኔ ጋር ነበር። “ይቅርታ እዛው ጠረጴዛ ላይ የተውኩት መስሎኝ ነው” በማለት ቁልፉን በእጄ እንደያዙኩ፤ ዋና አስተባባሪው “አምጣው!” በማለት፤ “እዛው እንገናኝ እኔ መኪናውን ይዤ እመጣለሁ። ሂዱ!” … ጉዞ ወደ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሆነ ፤…. 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደገባን፤ አስቀድሞ በተዘጋጀ ቢሮ አስገብተው፤ ለሚመለከተው አካል ሊያገናኙን የፈለጉ ቢሆንም፤ የቢሮው ሰውዬ በቦታው ባለመኖሩ እዛው ኮሪደር ላይ እንድንቆይ ተደረገ። ይዘውን የሄዱት ፖሊሶች ያለ ማቋረጥ በእጅ ስልካቸው ይደዋወላሉ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ጊዜው እየሄደ መጣ… ይዘውን ከሄዱት ፖሊሶች መካከል አንዱ የእኔን መንጃ ፍቃድ እና የናቲን መታወቂያ በእጅ ስልኩ ፎቶ በማንሳት፤ አድራሻችን በማስታወሻ ደብተር መዘገበ። አሁንም ተደጋጋሚ የሆነው የስልክ ግንኙነት እንደቀጠለ ነው።…. በዚህ መሓል ይህን ክትትል የሚመራው ዋናው አስተባባሪ “ይድኔ ብዙ ጊዜ አንተን የማውቅህ በሚዲያ ነው። ዛሬ ገና ነው በአካል ያየሁኽ። ናቲ እንኳን ከሆነ ጊዜ በኋላ እዚህ ቤቱ ሆኗል። እኛ ሥራ ላይ ነን። የተሰጠንን ሥራ እየሰራን ነው። ያዘዛችሁት ምግብ ሳትበሉ በሆነው ነገር ይቅርታ።…” እያለ ቀጥሎ ሊነግረን የነበረውን ነገር ሳይጨርስ የእጅ ስልኩ በመጥራቱ፤ የጀመረውን ወሬ ሳይጨርስ “ሀሎ…ሀሎ…” እያለ ከአጠገባችን እራቅ ብሎ ስልኩን ማውራት ቀጠለ ፤…. ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፤ የጀመረውን ንግግር በስልክ ጥሪ ምክንያት ያቋረጠው ዋናው ፤ ወደ እኛ በመምጣት ” ይድኔ አንተ ሂድ። መሄድ ትችላለህ። እኛ የታዘዝነውን ነው የምናደርገው። ሂድ!…” በማለት በሩን አመላከቱኝ ፤…

Source: Link to the Post

Leave a Reply