የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ውሳኔ አሳለፈ የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 21 2013 ዓ/ም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ…

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ውሳኔ አሳለፈ የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 21 2013 ዓ/ም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ…

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ውሳኔ አሳለፈ የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 21 2013 ዓ/ም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ትናንት ታህሳስ 20/2013 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ በሀገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጎ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዬች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ወሳኔ አስተላልፏል፡፡ ለሰላማዊ ሰልፉ መካሄድ አራት መሰረታዊ ጭብጦች የተዘረዘሩ ሲሆን እነርሱም በሀገራችን ኢትዮጵያ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በተደጋጋሚ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ/መተከል አካባቢ፣በወለጋ፣በጉራ ፈርዳና በደቡብ የሀገራችን ክፍልም በሰገን ህዝቦች ቀጣና አካባቢ በጉማይዴ ህዝብ ላይ የተካሄደውን የዘር ማጥፋትን በመቃወም፤ የሱዳንን የድንበር ጥሰት በመቃወም፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ስለሚገነባቸው ግንባታዎች ጉዳይ እና ስለ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስር እና ዳተኛ ስለሆነው የፍትህ ሂደት ሰላማዊ ሰልፍ ለጥር 09/2013 ዓ.ም. የተጠራ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፉን የሚያስተባብር ግብረ – ኃይልም አቋቁሟል፡፡ ግብረ – ኃይሉም በሚቀጥሉት ቀናት ዝርዝር ተግባራትን ያሳውቃል ሲል ባልደራስ ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply