የባልደራስ መኢአድ ቅንጅት ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች በቃሊቲ ማ/ቤት የሚገኙ የባልደራስ አመራሮች በዋናነት ከሁለት ወራት በፊት በወለጋ ጉሊሶ፣ ከአንድ ወር በፊት በማይካድ…

የባልደራስ መኢአድ ቅንጅት ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች በቃሊቲ ማ/ቤት የሚገኙ የባልደራስ አመራሮች በዋናነት ከሁለት ወራት በፊት በወለጋ ጉሊሶ፣ ከአንድ ወር በፊት በማይካድ…

የባልደራስ መኢአድ ቅንጅት ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች በቃሊቲ ማ/ቤት የሚገኙ የባልደራስ አመራሮች በዋናነት ከሁለት ወራት በፊት በወለጋ ጉሊሶ፣ ከአንድ ወር በፊት በማይካድራ፣ከሰሞኑ ደግሞ በመተከል እና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈፀሙ አሰቃቂ የጅምላ ጥቃቶችን በማውገዝ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከታጋይ አስቴር ስዩም ባለቤት መ/ር በለጠ ጌትነትና ከቤተሰቦች ጋር በመሆን ወደ ቃሊቲ ማ/ቤት በማቅናት የባልደራስ አመራሮችን ጠይቋል። በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ያነጋገርናቸው የባልደራስ መኢአድ ቅንጅት ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋና ስንታየሁ ቸኮል፣አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ከሁለት ወራት በፊት በወለጋ ጉሊሶ፣ከአንድ ወር በፊት በማይካድራ እንዲሁም ታህሳስ 13ለ14 ደግሞ በመተከል ቡለን ወረዳ በኩጅ በተባለ ቀበሌ በዋናነት በአማራዎች በተጨማሪም በሺናሻ፣በኦሮሞና በሌሎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ ተፈፀመውን የጅምላ ፍጅት በመጥቀስ አውግዘዋል፣የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘንም ገልፀዋል። የዘር ፍጅት በኢትዮጵያ ወደ ከፋ ደረጃ ከመሄዱ በፊት አስፈላጊ የሆነ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግና እርምጃም እንዲወሰድ ለፌደራል መንግስት፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ለሚኖሩ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች፣ለሚዲያ ተቋማትና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጭምር ጥሪ እና ምክረ ሀሳብ ሲያቀርቡ የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋ በወለጋ ጉሊሶ፣በማይካድራም፣ በመተከል ሆነ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ያሉ የዘር ፍጅቶች ሀገራዊ ችግር በመሆናቸው የጋራ ሀገራዊ መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል። አቶ እስክንድር ነጋ ኢትዮጵያ ትናንትና ዛሬ የገጠማትንና ነገም ሊገጥማት ይችላል ያሏቸውን ፈተናዎች በ3 ከፍለው አስረድተዋል። ይኸውም ባለፉት በርካታ ዓመታት የገጠማት ዘርፈ ብዙ ፈተና፣ አሁንን ጨምሮ በተለይም ባለፉት 2 እና 3 ዓመታት የገጠማት ምስቅልቅሎሽ እና ለወደፊቱ የሚጠብቃት ፈተናዎች በሚል የከፈሉት አቶ እስክንድር ያለፈውና የአሁኑ ምንም እንኳ አሰቃቂም ቢሆን ለችግሮቻችን ዘላቂ እና ስር ነቀል መፍትሄ እየሰጠን ካልሄድን የሆነብን ነገር ገና ከሚሆንብን ያነሰ እንጅ የበለጠ ሊሆን አይችልም ብለዋል። ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ፍጅት እና ሌሎች እንደ ሀገር ከባድ ዋጋ የሚያስከፍሉን ፈተናዎች ሊስተካከሉ የሚችሉት ከጥገናዊ ትግል ወጥተን የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ጠንክረን እና ተባብረን ስንሰራ ስለመሆኑ አስምረውበታል። በተመሳሳይ የባልደራስ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩሉ በማይካድራና በመተከል በአማራ እና በሌሎች ሰላማዊ ወገኖች ላይ የተፈፀመው እልቂት እጅግ እንዳሳዘነው ገልጾ ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤው ለመግደያነት እያገለገለ ያለው ከፋፋዩ ህገ መንግስትና በተግባር ያልተለወጠውና ለመለወጥም ያልፈለገው መንግስታዊ መዋቅሩ ነው ሲል ከሷል። “ጌታቸው ረዳ ቢሄድም በአካል አምሳሉ የሰራው ሌላኛው ጌታቸው ረዳ አለ” ያለው ስንታየሁ ሕወሓት ተመታ ቢባልም የሕወሓትን ጥፋት እንደ መልካም ነገር ቆጥሮ በእጥፍ የሚያስቀጥል ተረኛ አካሄድ እንጅ ለውጥ ሲመጣ እያየን አይደለም ብሏል። መፍትሄውም በመተባበርና በአንድነት መንፈስ ህዝባዊ ትግሉን በማጠናከር ነጻነትና ክብርን ማረጋገጥ ስለመሆኑ ጠቁሟል። በእለቱ አግኝተን ካነጋገርናቸው የባልደራስ አመራሮች መካከል የክፍለ ከተሞች አደራጅ ወ/ሮ አስቴር/ቀለብ ስዩም አንዷ ስትሆን አስቴር ካጋጠማት የጀርባ ህመም ጋር በተያያዘ ተገቢ የህክምና ትብብር ባለማግኘቷ ለወራት እየተሰቃየች መሆኗን ገልጻ ከብዙ መጉላላት በኋላ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በሰጠው ውሳኔ መሰረት በነገው እለት በግል ለመታከም ቀጠሮ የተሰጣት መሆኑን አስታውቃለች። አስቴር ያ ሁሉ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ ነጻነት፣ክብር፣አብሮነት፣እኩልነትና ፍትህ እውን ሊሆን ነው በሚል የሰነቅነውን ተስፋ የሚያጨልሙ የዘር ፍጅቶችን መመልከታችን ልብ ሰባሪ ስለመሆኑ ተናግራለች። የስም ለውጥ እንጅ የግብር ለውጥ የሌላቸው ፅንፈኛ፣ተረኛ፣ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ ኦህዴዶች ከኦነግ ሸኔ ጋር በመሆን በወለጋ ጉሊሶ፣በሆሮ ጉድሮ፣ በመተከል እና በሌሎችም የሚፈፅሙትን ዘግናኝ አማራ ተኮር ጭፍጨፋንና በአዲስ አበባ ከተማ፣በተቋማት እና በሌላም አካባቢ የሚያሳዩትን የለየለት የተረኝነት፣የአግላይነት፣የጠቅላይነትና የስግብግብነት አሳዛኝ አካሄድን ስንመለከት እንደ ሀገር የሚጠብቀን ፈተና ገና ብዙ መሆኑን ያሳያል ነው ያለችው። ሱዳን ሉአላዊነትን በመዳፈር በጎንደር ቋራ፣ በመተማ እና በምዕራብ አርማጭሆ በኩል የሚፈፅመው ወረራ፣ማፈናቀልና ዝርፊያ፣ በወለጋና በመተከል የሚፈፀመው አማራ ተኮር እልቂት የሕወሓት አመራሮች ለአማራ በእየአቅጣጫው የቤት ስራ እንደሰጡት የተናገሩትን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው ስትልም አክላለች። አስቴር ማይካድራን ጨምሮ በመተከል እንዲሁም በወለጋ በተለይም ደግሞ በጉሊሶ ላለቀው ወገናችን የተሰማትን ሀዘን በመግለፅ በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ ለውጥ እንዲመጣ ውድ ህይወታቸውን የከፈሉ ጀግኖችን እና በግዳጅ ተሰልፈው ከሃዲውን በመምታት በደማቸው ድል ያስመዘገቡ አካላትን ሁሉ አመሰግናለች። በተለይም በሕወሓት መራሹ ስርዓት ታስረው ለዓመታት በእስር ሲማቅቁ ቆይተው ከተፈቱ በኋላም በአቋማቸው ፀንተው ነፍሰ ገዳዩን ቡድን በመፋለምና ድል በማድረግ ከተሰውት ጀግና አማራዎች መካከል እነ አቶ ሀይሌ ማሞ፣ጎይቶም እርስቃይና ሌሎችም ፈፅሞ ከልቧ እንደማይወጡ ተናግራለች። ህዝቡም መዳረሻውን ነጻነትና ክብር በማድረግ ትግሉን እንዲያስቀጥል ነው መልዕክት ያስተላለፈችው። ከአስቴር በተጨማሪ ሌላኛዋ በቃሊቲ ማ/ቤት በእስር ላይ የምትገኘው አስካለ ደምሌም በመተከልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ መዋቅራዊና ህገ መንግስታዊ ጭምር ስለመሆኑ በማስረዳት የተሰማትን ልባዊ ሀዘን ገልጣለች። አስካለ ደምሌ ከመታሰሯ በፊት አንዳንድ የመንግስት እና የደህንነት አካላት በተደጋጋሚ መውጫ መግቢያ በማሳጣት ሲያደርሱባት የነበረውን በደል ተቋቁማ ከባልደራስ ጋር በፅናት ወደፊት በመቀጠሏ ዛሬ ላይ ያለጥፋቷ በእስር እየማቀቀች መሆኗን አስረድታለች። መጀመሪያ ላይ መንግስት በቂ ደመወዝ እየከፈላት መሆኑን በመጥቀስ ከባልደራስ ፓርቲ እንድትወጣ ሲወተውቱ ቆይተዋል፤ በገንዘብም ለማማለልና ከትግሉ ለማስወጣት ጥረት አድርገዋል፣ ወደ ውጭ ሀገር እንላክሽ ሲሉ በተለያዩ አካላት ቢጠይቁኝም ፈቃደኛ ባለመሆኔ ነው የታሰርኩት ብላለች። በመንግስት አቃቢ ህግ የቀረበባቸው ክስ ሆንተብሎ ባልደራስንም ሆነ አመራሮችን ከህዝብ ለመነጠልና ህዝብን ለመከፋፈል በዚህም የፖለቲካ ትርፍ አገኛለሁ ብሎ ከማለም የተደረገ ቢሆንም ትናንትም ሆነ ዛሬ እየተሸነፈ ይገኛል፤ ህዝቡም እውነቱ የትጋ እንዳለ ጠንቅቆ ያውቃል ነው ያለችው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply