You are currently viewing የባልደራስ ምክትል ፕሬዘዳንት በፖሊስ ታፍነው ተወስደዋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…

የባልደራስ ምክትል ፕሬዘዳንት በፖሊስ ታፍነው ተወስደዋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…

የባልደራስ ምክትል ፕሬዘዳንት በፖሊስ ታፍነው ተወስደዋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አምሃ ዳኘው ዛሬ መጋቢት 02/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ሲቪል በለበሱ የበኦህዴድ ብልጽግና አፋኝ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ አቶ አምሃ ዳኘው የታሠሩት የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን እሁድ መጋቢት 03/2015 ዓ.ም. ለማካሄድ ከአንድ ቀን ያነሰ ጊዜ በቀረበት ወቅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የባልደራስ ምክትል ፕሬዘዳንት የዕሁዱን የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅት ለማጠናቀቅ በጽ/ቤት እና በተለያዩ ሥፍራዎች ሥራቸውን እያከናወኑ ባሉበት ወቅት ከባልደራስ ቢሮ ህንጻ ሥር በመጠባበቅ ላይ በሚገኙ የደንብ ልብስ ባለበሱ እና ነጭ ፒክ አፕ መኪና በያዙ ግለሰቦች ተይዘው ተወስደዋል፡፡ አቶ አምሃ ዳኘው በአሁን ሰዓት ላዛሪስት አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ባልደራስ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply