# የባልደራስ አመራሮች ህዝባዊ ስብሰባ እንዳያደርጉ ቢከለከሉም አርባ ምንጭ ገቡ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 12/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ # የባልደራስ የሀገር አቀፍ ፊ…

# የባልደራስ አመራሮች ህዝባዊ ስብሰባ እንዳያደርጉ ቢከለከሉም አርባ ምንጭ ገቡ! ባህርዳር:- ሚያዚያ 12/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ # የባልደራስ የሀገር አቀፍ ፊርማ ንቅናቄ በደቡብ ክልል ተጀምሯል! / የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ደቡብ ኢትዮጵያ፤ አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል። አመራሮቹ ወደ ቦታው ያቀኑት ባልደራስ ሀገራዊ ፓርቲ መሆኑን አስመልክቶ በአካባቢው የሚደረገውን የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ንቅናቄ ለማስጀመር ነው። ድርጅቱ የፊርማ አሰባሰቡን ንቅናቄ ለማስጀመር በአርባ ምንጨ እና በወላይታ ሶዶ ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ ጠይቆ ከተፈቀደ ቦኃላ፣ “ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው” በሚል ስብሰባዎቹ እንዳይደረጉ ተከልክለዋል። ይህን አስመልክተው የተናገሩት የድርጅቱ ፕሬዚዳንት፣ “ስብሰባ ሊከለክሉን ይችላሉ፧ አርባ ምንጭ እንዳንመጣ ግን ሊከለክሉን አይችሉም፤ እንዳንመጣ ቢፈልጉም እኛ ግን የማንንም ፍቃድ ሳንጠይቅ መጥተናል”ብለዋል። አቶ ስንታየሁ በበኩላቸው፣ “አዳራሽ ብንከለከልም፣ የአርባ ምንጭ ህዝብ ግን ተቀብሎ የፊርማ አሰባሰቡን ንቅናቄ አስጀምሯል” ብለዋል። አቶ እስክንድር እና አቶ ስንታየሁ አርባ ምንጭ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በቅርቡ የተቋቋመው የፓርቲው የአርባ ምንጭ ኮሚቴ አቀባበል አድርጎላቸዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA Telegram (https://t.me/asharamedia24) Ashara Media – አሻራ ሚዲያ ስልክ፥ +251984000629 ዩትዩብ፥ https://bit.ly/33XmKr

Source: Link to the Post

Leave a Reply