You are currently viewing የባልደራስ አመራሮች ስለ አዲስ አበባ ወጣቶች ጅምላ እስር ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወያዩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ…

የባልደራስ አመራሮች ስለ አዲስ አበባ ወጣቶች ጅምላ እስር ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወያዩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ…

የባልደራስ አመራሮች ስለ አዲስ አበባ ወጣቶች ጅምላ እስር ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወያዩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ እና የውጭ ግንኙት ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን ተሰማ፣ የአሜሪካን ኤምባሲ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምክትል ካውንስለር ከሆኑት ከሚ/ር ኦስማን ኦዝታት ጋር አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ በመገኘት ተወያይቷል። የመንግሥት ኃይሎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የአድዋና የካራማራ ድል በዓላት ለማክበር በወጡ የባልደራስ አባላት እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ እያደረሱ ስላሉት እስር፣ ማዋከብ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ በጥልቀት ተወያይተዋል፡፡ እስረኞቹን በተመለከተ፣ ኤምባሲው የፍትህ ሚኒስቴርን በማነጋገር በቅርበት እንደሚከታተል አማካሪው ሚ/ር ኡስማን ለፓርቲው ልዑክ ተናግረዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ጥሰቱን በተመለከተ፣ በአዲስ አበባ ብቻ እየተፈፀመ ስላልሆነ፣ በሁሉም ክልሎች እየተፈፀሙ ያሉትን ጥሰቶች አካተው በቅርቡ ግልጽ የሆነ መግለጫ ኤምባሲው እንደሚያወጣ አማካሪው ገልፀዋል፡፡ ስለ ምክክር ኮሚሽኑ:_ በተጨማሪም፣ የፓርቲው ልዑክ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑን በተመለከተ በሰጠው ገለፃ፣ አማካሪ ኮሚሽኑ የተመሠረተበት ሂደት ባለድርሻ አካላትን ያላሳተፈ አና ብልጽግና ፓርቲ ብቻውን እና ለራሱ እንሚመቸው አድርጎ ያቋቋመው በመሆኑ፣ አገሪቱ ከኮሚሽኑ የምትጠብቀውን መፍትሄዎች እንዳያመጣ የሚያደርገው መሆኑን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ ስለኦነግ/ሽኔና በመንግሥት ውስጥ ስላሉት ሰርጎ ገቦች:_ ልዑኩ በወለጋ፣ በምዕራብ ሸዋ እና በቤንሻንጉል ክልል በኦነግ/ሸኔ፣ በቤንሻንጉል ታጣቂዎች እና በመንግሥት መዋቅሩ ውስጥ ባሉ ሰርጎ ገቦች እየተፈፀመ ስላለው የዘር ማጽዳት እና ማፈናቀል በዝርዝር ለኤምባሲው አማካሪ ያስረዳ ሲሆን፣ አማካሪውም በበኩላቸው ይህንን አቤቱታ ከሌሎችም የደረሳቸው መሆኑን ገልፀው፣ በባልደራስ በኩል ያሉትን ተጨባጭ የሰውም ሆነ የቪዲዮ ማስረጃዎች እንዲያቅርብ ጠይቀዋል፡፡ ልዑኩም ያሉትን ማስረጃዎች በሙሉ እንደሚያቀርቡ ቃል በመግባት ውይይታቸውን ፈጽመዋል ብሏል ባልደራስ በማህበራዊ ትስስር ገጹ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply