You are currently viewing የባልደራስ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ ፍርድ ቤት ቀረበ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ ናትናኤል ያለምዘውድ ታህሳስ 5/2015…

የባልደራስ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ ፍርድ ቤት ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ናትናኤል ያለምዘውድ ታህሳስ 5/2015…

የባልደራስ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ ፍርድ ቤት ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ናትናኤል ያለምዘውድ ታህሳስ 5/2015 በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ 3ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ በትምህርት ቤቶች ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በማሰብ በአዲስአበባ አበባ የኦሮምያ ባንዲራ አይሰቀልም በሚል ተማሪዎችን የተማሪ ወላጆችንና መምህራንን ቀስቅሷል ሲል የተጠረጠረበት ወንጀል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ስለሆነም ክስ ለመመስረት እንዲቻል ተጨማሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ 14 የምርመራ ቀናት የጠየቀ ሲሆን በናትናኤል ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ በኩል የተጠረጠረበትን ወንጀል አለመፈፀሙንና የቀረበበት አቤቱታም የዋስትና መብት የማያስከለክለው በመሆኑ በዋስ ተፈቶ ጉዳዩን እንዲከታተል ተጠይቋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ዘጠኝ የምርመራ ቀናት በመፍቀድ ለ ታህሳስ 14/ 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ሮሃ ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply