You are currently viewing የባልደራስ ከፍተኛ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል በ15 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲወጣ የቡራዩ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወስኗል።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም…

የባልደራስ ከፍተኛ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል በ15 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲወጣ የቡራዩ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወስኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም…

የባልደራስ ከፍተኛ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል በ15 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲወጣ የቡራዩ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወስኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ከፍተኛ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ በ3/2/2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ቡራዩ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቧል። ፍ/ቤቱም ለሶስት ወር የሚቆይ 20 ሺ ብር ዋስትና ከፍለዉ መዉጣት ይችላሉ ሲል መፍቀዱ ተገልጧል። የግፍ እስረኛዉ አቶ ስንታየሁም ፍ/ቤት ከዚህ በፊት 140 ሺ ብር በላይ የዋስትና ገንዘብ ከፍያለሁ ቢቻል በነጻ ልሰናበት ይገባል ሲል ተከራክራ ል። ችሎቱም የመጨረሻ 15 ሺህ ብር አድረጌልሃለዉ በማለት በዋስትና ከእስር እንዲፈታ ውሳኔ አስተላልፏል። ጉዳዩን ሲከታተል የቆዬው በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ቡራዩ ከፍተኛ ፍ/ቤት 15 ሽህ ብር ከፍሎ እንዲወጣ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ የክፍያ ሂደቱ እየተከናወነ መሆኑን በችሎቱ መገኘቷን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከገለጸችው ከአስካለ ደምሌ ለመረዳት ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply