የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ወደ ጃን ሜዳ በማቅናት አካባቢውን አፀዱ፤ አዲስ አበባን ጽዱ በማድረግ በኩልም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳ…

የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ወደ ጃን ሜዳ በማቅናት አካባቢውን አፀዱ፤ አዲስ አበባን ጽዱ በማድረግ በኩልም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጃን ሜዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አመታዊ ታላቅ ሃይማኖታዊ በዓል የሆነውን የጥምቀት በዓልን በየአመቱ የምታከብርበት ስፍራ መሆኑ ይታወቃል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ኗሪዎችና ከተማ መስተዳድሩ የተለያዩ ስፖርታዊ ፌስቲቫሎችን በቅጥር ግቢው በተለያዩ ጊዚያት ያካሂዱበታል። ይሁን እንጅ ከወራት በፊት ከተማ አስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ሰበብ በማድረግ ለተለያዩ ነጋዴዎች ለአትክልት መሸጫ ስፍራ ይሆን ዘንድ ነዋሪውን፣ምዕመናኑን እንዲሁም ቤተ ክርስትያኗን ሳያስፈቅድ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ለነጋዴዎች ስፍራውን ማሰረከቡ ይታወሳል። ይህን ህገ ወጥ ድርጊት ባልደራስ ቀድሞ ማውገዙ ተወስቷል። በዛሬው ዕለት ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ደግሞ ባልደራስ የፓርቲውን የፖለቲካ ተጠሪ ኢ/ር ጌታነህ ባልቻን ጨምሮ ሌሎች የከፍለ ከተማ አመራሮችንና አባላቱን በማስተባበር በጃን ሜዳ በመገኝት የመጀመሪያውን ዙር የፅዳት መርሃ ግብር ከውኗል። በቀጣይ የጃን ሜዳ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት የሚመለከተው ሁሉ እንዲያፀዳ በታላቅ አክብሮት በመጠየቅ ባልደራስ የመሪነት ሚናውን ቢወጣም በቀጣይ በሁሉም አካባቢዎች በጎ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያላሳለሰ ጥረት ያደርጋል ስለመባሉ የባልደራስ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply