የባልደራስ የቀድሞው መሪ እስክንድር ነጋ ከእስር መለቀቅ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-769b-08db18fbe1a2_tv_w800_h450.jpg

በቅርቡ ራሳቸውን ከፖለቲካ ማግለላቸውን የገለጹት አቶ እስክንድር ነጋ ከሁለት ቀናት እስር በኋላ በትናንትናው ዕለት ተለቀዋል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ መስራች እና የፓርቲው ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋ የካቲት 17/2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ከቆዩ በኋላ ትላንት መለቀቃቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቀለብ የቀድሞው የባልደራስ መሪ “በቁጥጥር ስር የዋሉት ምንም አይነት የእስር ማዘዣ ሳይወጣባቸው እና የተለቀቁትም ለፍርድም ሳይቀርቡ ነው” ያሉት ወ/ሮ ቀለብ፣ ተጨማሪ አስተያየት ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡

ስለ አቶ እስክንድር እስርም ሆነ ከእስር የመለቀቃቸው ጉዳይ በመንግሥት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply