You are currently viewing # የባልደራሷ አስካለ ደምሌ ደህንነቷ አደጋ ላይ መሆኑን  ተናገረች! ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሰሞኑ የመንግስት ሃይሎች የተለመደውን አፈና ለመፈፀም  እየተከታተሉኝ ነው…

# የባልደራሷ አስካለ ደምሌ ደህንነቷ አደጋ ላይ መሆኑን ተናገረች! ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሰሞኑ የመንግስት ሃይሎች የተለመደውን አፈና ለመፈፀም እየተከታተሉኝ ነው…

# የባልደራሷ አስካለ ደምሌ ደህንነቷ አደጋ ላይ መሆኑን ተናገረች! ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሰሞኑ የመንግስት ሃይሎች የተለመደውን አፈና ለመፈፀም እየተከታተሉኝ ነው ያለችው አስካል ደምሌ ደህነቶቹ ከምኖርበት ቤት አልፎ ቤተሰቦቸ ጋር እየሄዱ በቤተሰቦቼ ላይ ተፅኖ እያደረጉ ይገኛሉ ብላለች። ይህ ከመሆኑ በፊት በተለያዩ ስልኮች የማስፈራሪያ ዛቻ የደረሰብኝ ይገኛል። ከሰሞኑ በመንግስት መኪና ኮድ 4 ታረጋ ቁጥር 18376 6 ኪሎ አካባቢ መንገድ እየዘጉ ለማፈን ጥረት ቢያደረጉም ለጊዜዉ ሳይሳካላቸዉ ቀረተዋል። ለማፈን እንደ ምክንያት ካነሱት ዉስጥ አገር አፍራሹ ህገ ወጥ ቡድን አስካለ የመንግስት የዉስጥ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እያባከነች ነዉ ከእነዚህም ዉስጥ ከብዙ በጥቂቱ 1 በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ የታፈሱ ወጣቶች ወደ አዋሽ አረባ መጫናቸዉ ስማቸዉን በማዉጣት 2 የአማራ ተወላጅ የሆኑ የፀጥታ አካላት መታሰራቸዉን አስመልክቶ ከነ ስም ዝርዝራቸዉ በማዉጣት 3 በቃሊቲ እስር ቤት የአማራ ተወላጅ የሆኑ በዞን 5 የሚገኙ የወንድ እስረኞች በ12/5/2015 ዓ.ም መደብደባቸዉን ለሚድያ በመናገሬ 4 በቦሌ ቡልቡላ በኦህዴድ ስርዓት በጥይት የተመቱ በማዉጣቴና የህክምና አገልግሎት በመነፈጋቸዉ ይፋ ማድረጌ 5 ለቀናቶች ደብዛዉን በማጥፋት የአብን አመራር የሆነዉ አሸናፊ አካሉ ታፍኖ ባለበት በአማራ ክልል አባይ ማዶ የአማራ ልዩ ሃይል ካንፕ ዉስጥ የረሃብ አድማ ማድረጉን እና ኢ ኢሰብዓዊነት በጎደለዉ መልኩ መታሰሩን ይፋ ማድረጌ 6 ከአዲስ አበባ ከተማ ከከአስሪም ክ/ ከተማ የተወጣቱ የፀጥታ አካላት በፍቃደኝነት ወደ አማራ ክልል ሂደዉ ጥር 15/5/2015 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ በአገዛዙ ስርዓት መታፈናቸዉ እና ሌሎችም በአገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ፣ ሲታሰርና ሲፈናቀል እንደማንኛዉም ሰዉ ሰብዓዊነት የሚሰማዉ አካል ሁሉ ድምፅ በመሆኔ ከትግል ሜዳዉ ገለል ለማድረግ እና በድጋሚ እስር ቤት ለማስገባት እንደሆነ ያመላክታል ስትል ገልፃለች። በመጨረሻም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እያንዳንዱን ቤት እያንኳኳ የሚገኘዉን ስርዓት ህዝባዊ ትግል በማድረግ ልንታገለዉ ይገባል እኔም ከትግል ዓላማዩ መንገዴ ላፍታ እንኳን አልዘናጋም ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት መልክቷን ለአሻራ ሚዲያ አስተላልፋለች። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply