የባሕር ዳር ነዋሪዎች ለዋግኽምራ ወገኖቻቸው ድጋፍ እያሰበሰቡ ነው ባህርዳር:- መጋቢት 20/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የባሕር ዳር ከተማ በጎ አድራጎት ማኅበር ለዋግ…

የባሕር ዳር ነዋሪዎች ለዋግኽምራ ወገኖቻቸው ድጋፍ እያሰበሰቡ ነው ባህርዳር:- መጋቢት 20/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የባሕር ዳር ከተማ በጎ አድራጎት ማኅበር ለዋግኽምራ ወገኖች ድጋፍ ማሰባሰብ ጀምሯል። በበጎ አድራጎት ማኅበሩ 5 የተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ላይ ለዋግኽምራ ሕዝብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ድንኳኖች ተጥለዋል። የባሕር ዳር ነዋሪዎች በተተከሉት ድንኳኖች ምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦችን (ዱቄት፣ ፓስታ፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ…)፣ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስና ሌሎችንም ለነፍስ አድን ተግባር የሚረዱ ነገሮችን እንዲለግሱ ጥሪ ቀርቧል። ቀበሌ 13 ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል፣ ቀበሌ 14 ባለእግዚአብሔር ማዕድ ቁርጥ ቤት፣ ቀበሌ 2 በግተራ፣ ዓባይ ማዶ ገበያ ጉዛራ መድኃኒት ቤት እና ፖፒረስ ሆቴል በር የድጋፍ መቀበያዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply