የባሕር ዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ህይወቱ ማረፉ ተሰምቷል።

የባሕር ዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ህይወቱ ማረፉ ተሰምቷል።

በባሕር ዳር ከተማ ከሁለት ዓመታት በላይ ያሳለፈው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አለልኝ በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊት በድንገት ህይወቱ ማረፉ ታውቋል።

የአለልኝ አዘነ ስርዓተ ቀብር ዛሬ መጋቢት 18 በትውልድ ከተማው አርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ለማወቅ ተችሏል።

ከአርባምንጭ ከተማ ተስፋ ቡድን ተገኝቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ መጫወት የቻለው አለልኝ አዘነ በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን ሶስት ዓመታት በበባህር ዳር ቤት ግልጋሎት እየሰጠ ይገኝ ነበር።

አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዋናው ቡድን አንስቶ በተለያዩ የእድሜ እርከኖች መጫወት ችሏል።ኢትዮ ኤፍ ኤም ለወዳጆቹ ፣ ለዘመዶቹ ፣ ለጓደኞቹ ለክለብ አጋሮቹ እና ለመላው የእግር ኳስ ደጋፊዎች መፅናናትን እንመኛለን።

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply