የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን በጀት መመደቡን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ። ርዕሰ መስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/c2lZ6wivo9YWpawFTzjfyFYs9YRN2HQzujLleK_HzMpfwU2w3bA4Pq78qV86iaBuf0RMkGzeiJRL86cU31Zl9ukqh9pqrn6XAev4kgaxU193ib8Roy2HYjbxQBkHzjKVC1ThMRFzxjVe_iwGx462DLkyEBTuDxP7fCKJhm73HIAf3VHAnEsXgsskUiG-arNbpfZHX1V8BP3Sla8N6UVyQUksq4Z0756SoRePIcCXopU8knPq1WU45OZp2Xwip48aJdF0ruPd9x4zo8VH_rH1Hxw0ZUSuIiuN89gBdZxl-Syjwzb0O55uKvvtkkkPZ5-yv4WCPYeAJEcqwL2Z6t-CuA.jpg

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን በጀት መመደቡን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳደሩ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያለበትን ደረጃ ቦታው ድረስ ሄደው መመልከታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የስታዲየሙን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት አጠናቆ በአህጉር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዲሆን ለማድረግ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን የማጠናቀቂያ በጀት መድቧል ነው ያሉት፡፡

የክልሉን ሰላምና ጸጥታ በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናቆ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ዶክተር ይልቃል ጨምረው ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply