የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሠራቸኞቹ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባሕር ዳር ዩ…

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሠራቸኞቹ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የጥበበ ጊዮን ሪፈራል ሆስፒታል ለሰራተኞቹ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት መጀመር የሚያስችለውን ሰነድ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ታህሳስ 7 ቀን 2013ዓ.ም አፅድቋል፡፡ ሰነዱ መፅደቁ ሁሉንም ሰራተኞች የእድሉ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም በተለያየ ደረጃ እያገለገለ ያለውን የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ የእኔነት ስሜቱን የበለጠ እንዲያብብ እንደሚያደርገው እና ዩኒቨርሲቲው ራዕዩን ለማሳካት እያደረገ ያለውን ጉዞ እንደሚያፋጥነው ይታመናል ተብሏል፡፡ አሁን የፀደቀው ነፃ የህክምና እድል እስከ ሁለት አመት የሚያገለግል መሆኑን የገለፁት የዩኒቨርሲቲው የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተቀዳሚ ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ጥጋቡ ሰነዱ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ማሻሻያዎች ሊደረጉለት እንደሚችል ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ለሰራተኞች የሚደረገው ነፃ የህክምና ድጋፍ በአንድ የበጀት አመት እሰከ አስር ሺህ ብር ለሚሆን ወጭ ሙሉ በሙሉ መሸፈን የሚያስችል ሲሆን ከተጠቀሰው ብር በላይ ለሚሆን የህክምና ወጭ በፐርሰንት የሚሸፈን መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የህክምና አገልግሎቱ የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል ብቻ ሲሆን በሌላ ሰራተኛው በግሉ ወይም ከዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል አቅም በላይ በሆነ ሪፈራል በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር በሚገኝ የመንግስት ወይም የግል ተቋም ለሚደረግ ማንኛዉም አይነት የህክምና ወጭ አሁን በፀደቀው መመሪያ አይስተናገድም ተብሏል፡፡ ይህ ሰነድ ከሀሳብ ጀምሮ በተለያየ ደረጃ ለውጤታማነቱ የተሳተፉ አካላትን በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም እናመሰግናለን ብሏል ሆስፒታሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply