የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሀኪሞችን ቡድን ወደ ጋሸና ግንባር መላኩን አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ…

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሀኪሞችን ቡድን ወደ ጋሸና ግንባር መላኩን አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ ስፔሻሊስቶችን የያዘ የህክምና ቡድን ጋሸና ግንባር ወደሚገኙ የማገገሚያ ማዕከላት ልኳል፡፡ የህክምና ቡድኑ በጋሸና ግንባር የትግሬ ወራሪ ቡድን በፈጠረው ጦርነት ምክንያት የቆሰሉና ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ለማከም ተሰማርተዋል፡፡ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር የሽጌታ ገላው እንደገለጹት በጋሸና ግንባር ህክምና ለመስጠት የአጠቃላይ ቀዶ ህክምና፤ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስቶች፤ አንስቴዥያን፤ የጥርስ እና የስነ-አዕምሮ ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ያካተተ ቡድን ተሰማርቷል ብለዋል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ከ34 በላይ አባላትን የያዘ የሀኪሞች ቡድን ወደ ጋሸና ግንባር በተለያዩ ሁለት ቦታዎች የላከና ዘመቻው ለሁለት ሳምንት የሚቆይ መሆኑን ፕሮፌሰር የሽጌታ ገላው ተናግረዋል ብሏል ዩኒቨርስቲው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply