የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የሚረዳ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መድሐኒት መርጫ ሰራ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የሚረዳ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መድሐኒት መርጫ ሰራ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የሚረዳ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መድሐኒት መርጫ መስራቱን አስታወቀ፡፡
 
መድሃኒት መርጫው የተሰራው በኤልክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ፋኩልቲ መምህራኖች ነው ተብሏል፡፡
 
በኢትዮጵያ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ለመከላከል እንደሚያስችል የጠቀሰው ኢንስቲትዩቱ ለአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ማስረከቡንም ነው የገለጸው፡፡
 
ከዚህ ቀደም የነበረው መርጫ እስከ አምስት ሜትር ሲሆን አሁን የተሰራው እስከ አስራአምስት ሜትር ከፍታ መርጨት እንደሚችል ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

The post የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የሚረዳ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መድሐኒት መርጫ ሰራ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply