
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግሽ ተራራን በማልማት እውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ በድምቀት የተከበረውን አገር ዓቀፍ የግዮን በዓል አስምልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳን ዶ/ር ፍሬው ተገኘ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና ማህበረሰብ እንዲሁም የክልሉን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና የሚዲያ አካላትን በመያዝ ወደ ቦታው በማቅናት በዕለቱ የተከናዎኑ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ክዋኔዎችን ታድመዋል። አካባቢውን ለማልማት ከሚሰሩ ስራዎች በተጨማሪ የቦታውን ገናናነት እና ወደፊትም ለሀይማኖታዊ ቱሪዝም የሚያበረክተውን አስተዋፆ ይበልጥ ጎልቶ እንዲወጣ ከምንም በላይ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ተገልጿል፡፡ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰካላ ወረዳ በግሽ ተራራ እና አካባቢው ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎችን ሲሰራ ከመቆየቱም በላይ አካባቢውን ሀይማኖታዊ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ስራዎችን በስፋት እየሰራ ይገኛል፡፡ ጥር13/2015 ዓ.ም የተከበረውን የጻድቁ አቡነ ዘርዓ ብሩክ ዓመታዊ የንግስ በዓል ሲከበር ሊቃውንቱ የሚለብሱት 125 ሰማያዊ ካባ በልዩ ሁኔታ በማሰራት እና ከዓመታዊ የንግስ በዓሉ ጎን ለጎን ለግዮን በዓል ለሚሮጡ አትሌቶች ከ120 በላይ ቲሸርቶችን በመለገስ ዩኒቨርሲቲው ለቦታው እና ለቱሪዝም እድገት እንደሀገር የሚያደርገውን ተቋማዊ አስተዋፆ የክልል፤ የዞን እና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እውቅና ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ከምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር በልዩ ሁኔታ የተሰራ ካባ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝምና ቅርስ መምህር የሆኑት አቶ እንዳላማው ክንዴ በበኩላቸው አባይ የሚለውን ስያሜ በአቡነ ዘርዓ ብሩክ እንደወጣ እና ይህ ሐይማኖታዊ ቱሪዝም የበለጠ እንዲገለጥ በስፋት የማስተዋወቅ ስራ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ያለው ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ነው፡፡
Source: Link to the Post